አስተማማኝ ሰላምና ዘላቂ ኢኮኖሚያዊ እድገት የተረጋገጠባት፣ ዜጎች የዘር፣ የቋንቋ፣ የባህል፣ የሀይማኖት፣ የፖለቲካ አመለካከት ወዘተ ልዩነት ሳይደረግባቸው በብሄራዊ ጉዳዮች እኩል ሳተፉባትና ከልማቷ እኩል ተጠቃሚ የሚሆኑባት የበለጻገችና ዲሞክራሲያዊት ሀገር እውን ሆና ማየት፡፡
መልካም አስተዳደር እና የህግ የበላይነት የተረጋገጠባት፣ የፖለቲካ ስልጣን ከህዝብና ከህዝብ ብቻ የሚመነጭበት የፖለቲካ ባህል የዳበረባት፣ ዜጎች ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድሎችን ፍትሀዊ በሆነ መንገድ የሚጠቀሙባት ዴሞክራሲያዊ ስርዓት መገንባት፡፡
የሊበራል አስተሳሰብን ከሀገራችን ሁለንተናዊ እድገት ጋር አዋዶ ነባራዊ እና ተጨባጭ የፖለቲካ፣ ማህበራዊና ምጣኔ ሀብታዊ እውነታዎችን ከግምት ውስጥ በማስገባት ለዘብተኛ ሊበራሊዝም ርዕዮተ ዓለም ይከተላ
በከፍተኛ ፍጥነት በማደግ ላይ ያለው ኢኮኖሚ ለአጠቃላይ ብሄራዊ ምርት ያለው ድርሻ ከግብርናው ዘርፍ በልጧል፡፡ የአገልግሎት ዘርፉ ለዜጎች የስራ ዕድል በመፍጠርና እና የውጭ ባለሀብቶችን በመሳብ ያለው ድርሻ በየጊዜው እየጨመረ መጥቷል
የሰለጠነ የሰው ኃይል ለአንድ ሀገር ሁለንተናዊ ዕድገትና ብልጽግና ከሚያሰፈልጉ ግብዓቶች ዋነኛው ነው፡፡ የተማረ የሰው ኃይል ውስን የተፈጥሮ ሀብትን አቀናብሮ ፈጣንና ዘላቂ ልማት፣ ተረጋጋ የፖለቲካ ስርዓትና አስተማማኝ ሰላም፣ ፍትሀዊና ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ወዘተ ለመገንባት የማይተካ ድርሻ አለው
የሀገራችን የውጭ ጉዳይ ፖሊሲና ስታራቴጂ ዋነኛ ግብ በሀገር ውስጥ የሚደረገውን ኢኮኖሚያዊ፤ ፖለቲካዊና ማህበራዊ እቅዶችን ለማሳካት የሚደረውገን ጥረት ማገዝ ነው
ሰለ አጠቃላይ የፓርቲያችን ክህሎቶች እና የመሪዎቻችንን የተለያዩ መርጃዎች ይመልከቱ
ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ (ነእፓ)የሀገራችን እና የህዝባችን ችግሮች ምንጭ በዋናነት ፖለቲካዊ እንደሆነ እና መፍትሄውም በአብዛኛው ፖለቲካዊና አስተዳደራዊ እንደሆነ ያምናል፡፡ የመልካም አስተዳደር እጦት፣ አግላይ የፖለቲካ ስርዓት፣ ማኅበራዊ ፍትህ መጥፋት፣ አድሎ፣ ወገንተኛነት፣ ብሄርንና እምነትን መሰረት ያደረጉ ልምዶችና አሰራሮች የሀገራችን የፖለቲካ ስርዓት መገለጫዎች ሆነው ብዙ ዘመናት አልፈዋል፡፡
የሀገራችን አጠቃላይ ሁኔታ በወፍ በረር ይህንን በሚመስልበት ሁኔታ፣ ብዙ የአፍሪካ ሀገራትና መላው ዓለም በፈጣንና ሁሉን አቀፍ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊና፣ ስትራቴጂያዊ ለውጦች ውስጥ በማለፍ ላይ ይገኛሉ፡፡ በመረጃ እና ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ እድገት የሚመራው የለውጥ ሂደት በሀገራት፣ በህብረተሰብ እና በግለሰቦች መካካል ያለውን ግንኙነት በከፍተኛ ሁኔታ እንዲቀየር አድርጓል፡፡