ለምን #ብዕር

ለምን #ብዕር

****************************************************

የነጻነትና እኩልነት ፓርቲ ለትምህርትና አጠቃላይ የሰው ኃይል ልማት የሚሰጠው ትኩረት እጅግ ከፍተኛ ነው፡፡ ትምህርትና ስልጠና የአጠቃላይ ሀገር አቀፍ ልማት መሰረት ሆኖ የሚያገለግል ቁልፍ ዘርፍ ነው፡፡ ነእፓ ትምህርት ለሀገራችንና አጠቃላይ ለሰው ልጆች ስልጣኔ የተጫወተውን ቁልፍ ሚና ከግምት ውስጥ በማስገባትና በልማት ወደፊት የተራመዱ የዓለም ሀገራትን “ሚስጥረ-እድገት” በጥልቀት በመመርመር “ትምህርት-መር ብሄራዊ የልማት ስትራቴጂ” ለሀገራችን ሁለንተናዊ እድገት ወሳኝ ነው ብሎ ያምናል፡፡

ከዚህ እምነት በመነሳት ትምህርትና ስልጠናን ጨምሮ ሌሎች የሰው ኃይል ልማት ፕሮግራሞች የነእፓ ሀገራዊ የልማት ፍልስፍና እና ፖሊሲዎች የመሰረት ድንጋይ ሆነው ለሚቀጥሉት በርካታ አመታት ያገለግላሉ፡፡ ይህ ትምህርት-መር የልማት ስትራቴጂ ሀገራችንን በአጭር ግዜ ውስጥ ካለችበት አስከፊ ድህነት አላቆ መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገሮች መሀል ለማስገባት በሂደትም በዓለም ያደጉ አገሮች ክበብ ውስጥ ቦታ እንድትይዝ ዋነኛው የፖሊሲ ማዕቀፍ ሆኖ ያገለግላል፡፡

በዚህም መሰረት የትምህርት ዘርፍ የሀገራችን ሁለንተናዊ ልማት የመሰረት ድንጋይ በማድረግ ሁሉም የመንግስት የልማት ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች የሰው ኃይል ልማትን ያማከሉ ይሆናሉ፡፡

ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ ለትምህርት እና ለሰው ኃይል ልማት የሚሰጠውን ከፍተኛ ቦታ በተለያየ መንገድ ሲገልጽ ቆይቷል፡፡

ይህንኑ የፓርቲውን ትልቅ የፖሊሲ ማእቀፍ በምርጫ 2013 ወቅት ልዩ ትኩረት እንዲያገኘ የፓርቲው የምርጫ ምልክት ብዕር እንዲሆን ተወስኗል፡፡

ብዕር የትምህርት፣ የእውቀት እና የስልጣኔ ምልክት!

ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ

እኩልነት በተግባር!

ጥር 13፣ 2013

Comment:0