ዜና ነ.እ.ፓ

አዳዲስ ዜናዎችን ይከታተሉ!አዳዲስ ዜናዎችን ይከታተሉ!

Submitted by contenteditor@… on Wed, 03/18/2020 - 14:24

ላለፉት ሁለት ወራት በዓለም ዓቀፍ ደረጃ በፍጥነት በመዛመት አነጋጋሪ ሆኖ የቆየው የኮሮና ቫይረስ (COVID-19) በሃገራችን መታየቱ ዛሬ ከጤና ሚኒስቴር ተሰምቷል፡፡

በሽታው ዓለም ዓቀፍ ወረርሽኝ መሆኑንም ከአንድ ቀን በፊት የዓለም የጤና ድርጅት WHO ማወጁ ይታወሳል፡፡

በሽታው በፍጥነት እንዳይዛመት መግታት ቀዳሚው ተግባር በመሆኑ ሁሉም ኢትዮጵያዊ አስፈላጊውን የደህንነት ጥንቃቄዎች እንዲወስድ ማሳሰብ እንወዳለን፡፡

 

የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩትም ይህንን ወረርሽኝ የመዛመት ፍጥነቱን ለመቆጣጠር የሚያስችሉ መረጃዎችን እንደሚሰጥና ሌሎች ተግባራዊ እንቅስቃሴዎች እንዲሚያፋጥን ተስፋ እናደርጋለን፡፡

 

እንደ እነዚህ ያሉ ከባድ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙን እንደሁልጊዜው ኢትየጵያዊ እሴታችን መተሳሰብን ከፊት በማድረግ ከጤና አጠባበቅ ጋር የተያያዙ እንዲሁም ለየእለት ፍጆታ የሚውሉ ቁሳቁሶች አቅርቦትና ተደራሽነት ላይ ልንረባበረብ ይገባል፡፡

 

ሁኔታውን ተጠቅሞ አላስፈላጊ የዋጋ ጭማሪ ማድረግና ተያያዥ አስተሳሰቦች አጥፊ ናቸውና ልንርቃቸው ይገባል፡፡

 

ሁሉም ሃገርና ወገን ወዳድ ኢትዮጵያውያን ሂደቱን ለመቆጣጠር የሚያስችሉ ተግባራት ላይ ያለመታከት እንዲረባረቡም ወገናዊ ጥሪ እናስተላልፋለን፡፡

ነፃነትና እኩልነት ፓርቲ

news image
News Category