ዜና ነ.እ.ፓ

አዳዲስ ዜናዎችን ይከታተሉ!አዳዲስ ዜናዎችን ይከታተሉ!

Submitted bycontenteditor@… onTue, 11/08/2022 - 15:02

/ ኢሎና ኮሌ የነእፓን ዋና መስሪያ ቤት ጎበኙ፡፡

****************************************

በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ የፖለቲካ ጉዳይ ዘርፍ ባልደረባ የሆኑት / ኢሎና ኮሌ በዛሬው እለት የነእፓን ዋና መስሪያ ቤት ጎብኝተዋል፡፡ / ኢሎና ከነእፓ ሊቀመንበር / አብዱልቃድር አደም እና ከፓርቲው የፖለቲካ ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ኢብራሂም መሀመድ ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች እና በኢትዮጵያ እና አሜሪካ ሁለትዮሽ ግንኙነት ዙሪያ ሰፊ ውይይት አድርገዋል፡፡

ሀገራዊ ምክክር፣ በፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል ሊደረግው የታሰበው ውይይት (Inter Party Dialogue) እንዲሁም የአሜሪካ መንግስት በኢትዮጵያ ላይ ለመውሰድ ያሰባቸው ማእቀቦች ረቂቅ ህጎች (ኤችአር 6600 እና ኤስ 3199) በውይይት በስፋት የተዳሰሱ ጉዳዮች ናቸው፡፡

/ አብዱልቃድር ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ በሀገራችን አካታች ሀገራዊ ምክክር እንዲካሄድ እስከ አሁን ያደረገውን እንቅስቃሴ ገልጸው ሂደቱ እንዲሳካ ነእፓ ጥረቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል፡፡

/ ኢሎና በኢትዮጵያ ሊደረግ የታሰበው ሀገራዊ ምክክር በኢትዮጵያ አስተማማኝ ሰላም እና መረጋጋት ለማስፈን እጅግ አስፈላጊ እና ወቅታዊ መሆኑን ጠቅሰው ሀገራቸው ሂደቱን በቅርበት እንደምትከታተል ጠቅሰዋል፡፡

የአሜሪካ መንግስት በኢትዮጵያ ላይ የተለያዩ ማእቀቦች ለመጣል ያዘጋጃቸውን ረቂቅ ህጎች በተመለከተ እርምጃው ከከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣን ይበልጥ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ህይወት እንዳይጎዳ ነእፓ ከፍተኛ ስጋት ያለው መሆኑ ሊቀመንበሩ ገልጽው፣ መንግስታቸው ረቂቆቹንን በጥንቃቄ ሊያጤናቸው እንደሚገባ አስታውቀዋል፡፡

አቶ ኢብራሂም በሀገር ደረጃ የሚካሄደው ብሄራዊ ምክክርም ሆነ በፓርቲዎች መካከል ሊካሄድ የታሰበው ዉይይት በሀገራችን ለረዢም ዘመናት የቆዩ የፖለቲካ ቁርሾዎችን አርግቦ እርቅ እና ሰላም ለማስፈን መተኪያ የሌላቸው የፖለቲካ ሂደቶች መሆናቸውን እና በዚህ ሂደት ውስጥ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሚና እና ኃላፊነት ከፍተኛ መሆኑን አስምረዋል፡፡

በነእፓ አመራሮች እና በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ ኃላፊዎች ከዚህ ቀደም በርካታ ውይይቶች የተደረጉ ሲሆን ውይይቶቹ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማጠናከር አዎንታው አስተዋጽኦ ይኖራቸዋል ተብሎ ይገመታል፡፡

ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ

መጋቢት 22 2014

news image
News Category