ዜና ነ.እ.ፓ

አዳዲስ ዜናዎችን ይከታተሉ!አዳዲስ ዜናዎችን ይከታተሉ!

Submitted bycontenteditor@… onThu, 12/17/2020 - 12:18

ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ (ነእፓ) በመተዳደሪያ ደንቡ እና በአዲሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች አዋጅ መሰረት ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ባስቀመጠው የጊዜ ገደብ መሰረት ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤውን ለማካሄድ ዝግጅቱን ጀምሯል፡፡

በፓርቲው ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የተቋቋመው የጉባኤ አዘጋጅ አብይ ኮሚቴ በዛሬው እለት ባካሄደው ስብሰባ በረቂቅ የጉባኤው የስራ እቅድ ላይ የተወያየ ሲሆን ጉባኤው በጥር ወር መጨረሻ እንዲካሄድ ስምምነት ላይ ደርሷል፡፡ አብይ ኮሚቴው የሎጅስቲክ፣ የፋይናንስ፣ የጥሪ፣ የሚዲያ፣ የኪነጥበብ እና ሌሎች ልዩ ልዩ ንኡሳን ኮሚቴዎች እንደሚቋቋሙ አስታውቋል፡፡

የፓርቲው ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ ፓርቲው ከተመሰረት ጀምሮ ያካበተውን የተግባር ተሞክሮ መሰረት አድርጎ ነእፓን ከፍ ወዳለ እና ወደ ተሻለ ምዕራፍ ለማሻገር ወሳኝ ሁነት እንደሚሆን የጉባኤው አዘጋጅ ኮሚቴ ገልጿል፡፡

የኢትዮጰያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በአዋጅ ቁጥር 1162/2011 መሰረት የፖለቲካ ፓርቲዎች ጠቅላላ ጉባኤቸውን ማድረግ ያለባቸውን የጊዜ ገደብ ቀደም ሲል መግለጹ ይታወሳል፡፡

ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ (ነእፓ)

06 ታህሳስ 2013

news image
News Category