ዜና ነ.እ.ፓ

አዳዲስ ዜናዎችን ይከታተሉ!አዳዲስ ዜናዎችን ይከታተሉ!

Submitted bycontenteditor@… onTue, 11/08/2022 - 15:06

ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ አንደኛ መደበኛ ጉባኤውን በትናንት ዕለት እሁድ መጋቢት 18/2014 የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ታዛቢዎች በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ አካሂዷል፡፡ ጉባኤው የተሻሻለውን የፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ ላይ ተወያይቶ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል፤ የተጓደሉ የብሄራዊ ምክር ቤት አባላትንም ምርጫ አካሂዷል፡፡

ቀደም ሲል በነበረው መተዳደሪያ ደንብ መሰረት 35 የነበረው ማዕከላዊ ኮሚቴ ብሄራዊ ምክር ቤት በሚል የስያሜ ለውጥ አድርጎ አባላቱንም 10 አሳድጓል፡፡ በዚህም መሰረት 28 አዳዲስ ቋሚ የብሄራዊ ምክር ቤት አባላት በክልሎች እጩ አቅራቢነት ቀርበው በሚስጥር ድምጽ ተሰጥቶባቸዋል፡፡ በዚሁ መሰረት ጉባኤው 45 ቋሚና 15 ተለዋጭ አባላት ያሉት ብሄራዊ ምክር ቤት አጽድቋል፡፡

በጉባኤው 900 በላይ አባላት ከመላው ኢትዮጵያ የተሳተፉ ሲሆን የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች አመራሮች ተገኝተው የአጋርነት መልዕክቶቻቸውን አስተላልፈዋል፡፡

news image
News Category