ዜና ነ.እ.ፓ

አዳዲስ ዜናዎችን ይከታተሉ!አዳዲስ ዜናዎችን ይከታተሉ!

Submitted by contenteditor@… on Wed, 03/18/2020 - 14:26

ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ ሀገራዊ መግባባት/National Dialogue ለማስጀመር የሚያስችል ሰነድ ይፋ አደረገ፡፡

ነእፓ በሀገራችን ያሉ ዘርፈ ብዙ ፖለቲካዊ እና ማህበራዊ ችግሮችን ለማስወገድ እና በተለያዩ የፖለቲካ ሀይሎች መካከል መግባባትን ለመፍጠር ወሳኝ በሆኑ ሀገራዊ አጀንዳዎች ዙሪያ ሁሉን አቀፍ ውይይት እንዲካሄድ ጥሪ አቀረበ፡፡

የፓርቲው ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ባሳለፈ ውሳኔ መሰረት የሀገራችንን ሰላም እና የህዝቦቿን አንድነት አየተፈታተኑ ያሉ የደህንነት ስጋቶችን ለመቅረፍ ሰፊ መሰረት ያለው ውይይት እና መግባባት በአፋጣኝ መፈጠር አለበት፡፡

ፖለቲካዊ ተግዳሮቶቻችን እልባት ሳያገኙ ምርጫ ማካሄድ በሂደቱና በውጤቱ ላይ አሉታዊ ተጽእኖ እንደሚኖረው የገለጸው የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ፣ ብሄራዊ መግባባት መፍጠር አንገብጋቢ ሀገራዊ አጀንዳ መሆኑን አመልክቷል፡፡

የመግለጫው ሙሉ መልእክት በተያያዘው ጽሁፍ ተመልክቷል፡፡

ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ
መጋቢት 3 2012
አዲስ አበባ::

news image
News Category