ዜና ነ.እ.ፓ

አዳዲስ ዜናዎችን ይከታተሉ!አዳዲስ ዜናዎችን ይከታተሉ!

Submitted by contenteditor@… on Wed, 10/07/2020 - 10:55

ነእፓ በአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በጎርፍ ለተጎዱና ለተፈናቀሉ አርብቶ አደር ማህበረሰብ ድጋፍ የሚውል 150,000 (አንድ መቶ ሀምሳ ሺህ ብር) ድጋፍ አድርጓል፡፡ ድጋፉን የፓርቲው ሊቀመንበር / አብዱልቃድር አደም ለክልሉ ርእሰ መስተዳድር ለአቶ አወር አርባ ሰመራ ከተማ በመገኘት ለዚሁ በተዘጋጀው ስነስርአት ላይ አስረክበዋል፡፡

ሊቀመንበሩ ነእፓ ለሀገራችን የአርብቶ አደር ህዝቦች ሁለንተናዊ እድገት ከፍተኛ ትኩረት የሚሰጥ መሆኑን ገልጸው፣ የጎርፍ እና ሌሎች የተፈጥሮ አደጋዎችን ለመከላከል የፌዴራል እና የክልል መንግስታት ዘላቂ መፍትሄ ሊፈልጉ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

/ አብዱልቃድር የአፋር ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ አወል አራባ እና ካቢኔአቸው በአደጋው የተጎዱ ዜጎችን መልሶ ለማቋቋም እያደረጉ ያሉትን ጥረት አድንቀው፣ ነእፓ አቅሙ በፈቀደ መጠን ከክልል መስተዳድሩ ጎን እንደሚቆም አስታውቀዋል፡፡

በፕሮግራሙ ላይ ለተገኙት ለአቶ ኡመር አሊሚራህ እና ቤተሰቦቻቸው በሱልጣን ሀንፈሬ አሊሚራህ ህልፈት መላው የነእፓ ዓባላት እና አመራሮች የተሰማቸውን ከፍተኛ ሀዘን ገልጸዋል፡፡

ነእፓ ላደረገው ድጋፍ የክልል መስተዳድሩ የምስጋና እና የእውቅና የምስክር ወረቀት ሰጥቷል፡፡

ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ

መስከረም 24 2013

ሰመራ፡፡

news image