ዜና ነ.እ.ፓ

አዳዲስ ዜናዎችን ይከታተሉ!አዳዲስ ዜናዎችን ይከታተሉ!

Submitted bycontenteditor@… onTue, 06/01/2021 - 08:43

የአዲስ አበባ ጎዳናዎች በነእፓ የምርጫ ቅስቀሳ ደምቀው ዋሉ፡፡

*************************************************

የነጻነትና እኩልነት ፓርቲ አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ያዘጋጀው የጎዳና ላይ ቅስቀሳ በከተማዋ ዋና ዋና ጎዳናዎች በደማቅ ሁኔታ ተካሂዷል፡፡

በኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ እና በነእፓ አርማ በደመቁ ተሽከርካሪዎች በመታገዝ ሲካሄድ በዋለው የምርጫ ቅስቀሳ ፕሮግራም የከተማዋ መራጭ ነጻነትን፣ እኩልነትን፣ ፍትህን፣ አንድነትን፣ ወንድማማችነትን፣ እንዲመርጥ ከፍተኛ ቅስቀሳ ተድርጓል፡፡

ነእፓ የአዲስ አበባን ውስብስብ የመልካም አስተዳደር፣ የድህነት፣ የስራ አጥነት፣ የሰላም፣ የመኖሪያ ቤት፣ የትራንስፖርት፣ የጤና እና የትምህርት .... ችግሮች ለመፍታት የሚያስችለው የፖሊሲ አማራጮችን ይዞ ቀርቧል፡፡

ነእፓ ለአዲሳባ

“እኩልነት በተግባር”

ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ

news image
News Category