ዜና ነ.እ.ፓ

አዳዲስ ዜናዎችን ይከታተሉ!አዳዲስ ዜናዎችን ይከታተሉ!

Submitted by contenteditor@… on Thu, 11/05/2020 - 12:32

የአውሮፓ ህብረት የኢትዮጰያ ጉዳይ እንዳሳሰበው ገለጸ።

ብራስልስ፣ ኖቬምበር 22፣ 2020

የአውሮፓ ህብረት ከፍተኛ ተወካይ እና ምክትል ሊቀመንበር የሆኑት ጀሴፍ ቦረል በኢትዮጰያ ውስጥ የሚገኙ ሁሉም የፖለቲካ ኃይሎች እና የኢትዮጰያ ጎረቤቶች ውጥረትን እንዲያረግቡ፣ ግጭትን ከሚቀሰቅሱ ቃላት እና ወታደራዊ እንቅስቃሴዎች እንዲቆጠቡ አሳስበዋል። ይህንን አለማድረግ ሀገሪቱን እና አካባቢውን ለብጥብጥ የሚዳርግ መሆኑን ገልጸዋል።

ኃላፊው ሁሉን አቀፍ ብሄራዊ ውይይት በማድረግ ብሄራዊ መግባባት መፍጠር ከመቼውም ጊዜ በበለጠ አስፈላጊ መሆኑን አመልክተዋል። ብሄራዊ መግባባትን መፍጠር ኢትዮጰያውያን ዴሞክራሲያዊ እና የበለጸገች ሀገር እንዲኖራቸው ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል። በኢትዮጰያ ሰላም እና መረጋጋትን እውን ለማድረግ ኃይል እና ማስፈራራት መፍትሄ እንደማይሆን የገለጹት ኃላፊው፣ የኢትዮጰያ የለውጥ እንቅስቃሴ እንዲሳካ፣ በሀገሪቱ የህግ የበላይነት እንዲረጋገጥ እና እ.አ.አ በ2021 ይካሄዳል ተብሎ የሚጠበቀው ጠቅላላ ምርጫ በሰላም እንዲካሄድ የአውሮፓ ህብረት ድጋፉን እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።

news image
News Category