ዜና ነ.እ.ፓ

አዳዲስ ዜናዎችን ይከታተሉ!አዳዲስ ዜናዎችን ይከታተሉ!

Submitted by FEP@admin_123_ on Wed, 10/30/2019 - 16:47

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚንስትር ክቡር ዶ/ር አብይ አህመድ የ2019 የኖቤል የሰላም ተሸላሚ በመሆናቸው ነእፓ የተሰማው ታላቅ ደስታ ይገልጻል፡፡

ባለፉት 18 ወራት በሀገራችን እና በአካባቢያችን ሰላም እና መረጋጋት እንዲረጋገጥ ክቡር ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ  ላደረጉት አስተዋጾ ያገኙት ዓለም ዓቀፍ እውቅና በቀጣይ በሀገራችን ለመገንባት ለምናስበው ሰላም ከፍተኛ አስተዋጾ አለው፡፡ ሽልማቱ ህዝባችን የናፈቀውን አስተማማኝ ሰላም ማግኘት እና ማጣጣም ይችል ዘንድ ጠቅላይ ሚነስትሩ እና መስተዳድራቸው ከእስከ ዛሬው በበለጠ ጠንክረው እንዲሰሩ ትልቅ የስነልቦና ምርኩዝ  ይሆናቸዋል ብለን እናምናለን፡፡ ሽልማቱ ሀገራችን ወደ ዴሞክራሲያዊ ስርአት ለመሸጋገር ጥረት እያደረገች ባለበት እና ነጻ እና ፍትሀዊ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት በምታደርግበት ወቅት በመሆኑ ታሪካዊ ነው፡፡

ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ በሀገራችን አስተማማኝ ሰላም ለመገንባት የሚያደርገውን ጥረት ከመንግስት እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር በመስራት አጠናክሮ እንደሚቀጥል በዚህ አጋጣሚ ያረጋግጣል፡፡ 

news image
News Category