ዜና ነ.እ.ፓ

አዳዲስ ዜናዎችን ይከታተሉ!አዳዲስ ዜናዎችን ይከታተሉ!

Submitted by contenteditor@… on Mon, 06/15/2020 - 14:29

የሃይማኖት እኩልነት ለሀገር ሰላም እና እድገት የመሰረት ድንጋይ ነው!!

***************************************************************************************

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤትንና የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስልን በአዋጅ ማቋቋም በህገ መንግስት የሰፈረውን የሀይማኖት እኩልነት ያረጋገጠ ውሳኔ ነው፡፡

*******************************************************************************************

ኢትዮጵያ የተለያየ ባህል እና ሀይማኖት ያላቸው ህዝቦች በሰላም እና በፍቅር የሚኖሩባት ሀገር መሆኗ ይታወቃል፡፡ ክርስትና እና ኢስላም በኢትዮጵያ ታሪክ እና ሀገረ መንግስት ግንባታ ከፍተኛ ሚና ነበራቸው፡፡ ኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖች እና ሙስሊሞች በወንድማማችነት እና በመከባበር ለትውልድ የሚተላለፍ አኩሪ ታሪክ ባለቤት ናቸው፡፡ ከዚህ የአብሮነት ታሪክ በተጻራሪ በተለያየ ዘመን በሀገራችን የነገሱ መሪዎች አንዱን ከፍ ሌላውን ዝቅ የማድረግ ፖሊሲ ይከተሉ እንደነበር ታሪክ የሚመሰክረው ሀቅ ሲሆን በዚህም ምክንያት የዜጎች የእምነት እና የአምልኮ ነጻነት የተገደበባቸው አጋጣሚዎች አልፈዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የመደራጀት እና ህጋዊ እውቅና ያለው ሀገራዊ ተቋም የመፍጠር ዘመን ተሻጋሪ ህልም እውን ይሆን ዘንድ ተከታታይ ትውልዶች ለመንግስት ጥያቄ ሲያቀርቡ ቆይተዋል፡፡ የሙስሊሙ የእምነት አባቶች የመጅሊስ የህጋዊ እውቅና ጥያቄአቸውን ያለመታከት ለቀድሞ መንግስታት ሲያቀርቡ የቆዩ ቢሆንም ሰሚ ሳያገኝ ዛሬ ላይ ደርሰናል፡፡ ባለፉት ጥቂት አመታት የመንግስት የኃይማኖት ጣልቃ ገብነት እንዲቆም እና ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞችን የሚወክል ጠንካራ ብሄራዊ ተቋም እንዲቋቋም ከፍተኛ እንቅስቃሴ ተካሂዷል፡፡ ዛሬ ላይ የጸደቋው የመጅሊስ ማቋቋሚያ አዋጅ ተከታታይ ትውልዶች የከፈሉት ከፍተኛ ዋጋ ፍሬ ነው፡፡

በተመሳሳይ ህጋዊ ሰውነት እና እውቅና እንዲሰጣቸው ሲጠይቁ የኖሩ የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል አባል ኢትዮጵያዊያን ጥያቄአቸው በመንግስት ተቀባይነት እንዲያገኝ ለረዥም ዘመናት በትእግስት ቆይተው በዛሬው እለት ካውንስሉ በአዋጅ መቋቋሙ ታሪካዊ ነው፡፡

ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ (ነእፓ) ለመላው ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች እና ለኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል አባል ምእመናን፤ እንዲሁም በሀገራችን የኃይማኖት ነጻነት እና እኩልነት እንዲረጋገጥ ለታገሉ ኢትዮጵያውያን በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ ይላል፡፡ትግላችሁ ፍሬ አፍርቷል እና ደስ ሊላችሁ ይገባል፡፡

የዜጎችን የእኩልነት ጥያቄዎች ህጋዊ ምላሽ ሲያገኝ አንድነታችን ይጠነክራል፣ አብሮነታችን ይጎለብታል፣ ሰላማችን ይጠበቃል፣ የዜጎች የጋራ ጠላት ከሆነው ድህነት ለመላቀቅ እንደ ሀገር የምናደርገው ትግል በአጭር ጊዜ እንዲሳካ ዋስትና ይሠጣል፡፡

ሁለቱ የእምነት ተቋማት በአዋጅ የጸደቁበት የዛሬው እለት የእምነት እና የብሄር ልዩነቶቻችንን ተሻግረን የህዝቦች ሰብአዊ እና ዴሞክራሲያዊ መብቶች የሚከበርባት፣ ዜጎች በነጻነት እና በእኩልነት የሚኖሩባት ሰላማዊ ሀገር ለመገንባት በአዲስ መንፈስ የምንነሳበት ታሪካዊ እለት ነው፡፡

ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ

ሰኔ 4፣ 2012

Image removed.

Image removed.

Image removed.

1.6KArif Mohammed and 1.6K others

62 Comments

252 Shares

Like

Comment

Share

Comments

Most RelevantWrite a comment...

 

  •  
  •  
  •  
  •  

View comments

 

 

 

Freedom and Equality Party

June 10 at 12:35 PM  · 

Image removed.

 

ETHIO FM 107.8

June 10 at 12:17 PM  · 

ቀጣዩ አገር አቀፍ ምርጫ የኮሮና ቫይረስ ስጋት አለመሆኑ ከተረጋገጠበት ጊዜ አንስቶ ከዘጠኝ ወራት እስከ አንድ ዓመት ባሉት ጊዜ ውስጥ እንዲካሄድ ተወሰነ።

የፌዴሬሽን ምክር ቤት የኮሮና ቫይረስ ስርጭት በሃገሪቱ ስጋት ሆኖ እስከቀጠለ ድረስ ሁሉም የፌደራልና ክልል ምክር ቤቶች ስራቸውን እንዲቀጥሉ በሚል የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ አጽድቋል።

የፌዴሬሽን ምክር ቤት 5ኛ የፓርላማ ዘመን 5ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ 2ኛ መደበኛ ስብሰባ ዛሬ እያካሄደ ነው።

የምክር ቤቱ የሕገ መንግሥት ትርጉምና የማንነት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምርጫን ከማራዘም ጋር በተያያዘ የቀረበለትን የህገ መንግስት ትርጓሜ ጥያቄ ከአተረጓጎም ፣ መርህ ፣ ዘዴና አላማ ይዘት ጋር ገምግሞ ተገቢውን ምርመራ በማድረግ የውሳኔ ሃሳብ ማሳለፉን አስታውቋል።

1. የኮሮና ቫይረስ ስርጭት በሃገሪቱ ስጋት ሆኖ እስከቀጠለ ድረስ ሁሉም የፌደራልና ክልል ምክር ቤቶች ስራቸውን እንዲቀጥሉ ፣

2. ዓለም አቀፍና አህጉር አቀፍ የጤና ድርጅቶች ኮቪድ19ኝን በተመለከተ የሚያወጡትን መረጃ መሰረት በማድረግ የጤና ሚኒስቴር፣ የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እና የሳይንሱ ማህበረሰብ አካላት ወረርሽኙ የህዝብ ስጋት አለመሆኑን ካረጋገጡና ይህም በምክር ቤቱ ከፀደቀ ሃገራዊ ምርጫውን ከ9 ወር እስከ 1 አመት ማካሄድ እንደሚቻል የውሳኔ ሀሳብ አቅርቧል።

ኮሚቴው ያቀረበውን የውሳኔ ሀሳብም የፌዴሬሽን ምክር ቤት በማድመጥ እና በውሳኔው ላይ በመወያየት ኮሮና ቫይረስ ስርጭት በሃገሪቱ ስጋት ሆኖ እስከቀጠለ ድረስ ሁሉም የፌደራልና ክልል ምክር ቤቶች ስራቸውን እንዲቀጥሉ በሚል የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ አጽድቆታል።

የውሳኔ ሃሳቡ በአራት ተቃውሞ፣ በአንድ ድምጸ ተዓቅቦ እና በ114 ድጋፍ በአብላጫ ድምጽ መጽደቁን ምክር ቤቱ አስታውቋል።

የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሀም ከትናንት በስቲያ በገዛ ፍቃዳቸው ከሃላፊነታቸው መልቀቃቸውን ማስታወቃቸው ይታወሳል፡፡

ሆኖም በፌዴሬሽን ምክር ቤት አሰራር ዋና አፈ ጉባኤ ባይኖሩ ምክትሉ ስራውን መምራት ይችላል በሚለው ህግ መሰረት የዛሬው ጉባኤ በምክትል አፈ ጉባኤው እየተመራ ነው፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

ኢትዮ ኤፍ ኤም የኢትዮጵያዊያን

ሰኔ 3 ቀን 2012 ዓ.ም

News Category