የነእፓ ሊቀመንበር ከጃፓን አምባሳደር ጋር ተወያዩ፡፡
****************************************
የነጻነትና እኩልነት ፓርቲ ሊቀመንበር ዶ/ር አብዱልቃድር አደም በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ጋር ተገናኝተው በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አካሂደዋል፡፡
በውይይቱ ዶ/ር አብዱልቃድር የነጻነትና እኩልነት ፓርቲን ማህበረ-ፖለቲካ እና ኢኮኖሚያዊ እሳቤዎች፣ ነእፓ ባለፉት አመታት ያከናወናቸውን እንቅስቃሴዎች፣ እንዲሁም ሀገራዊ ምክክር እና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ የፓርቲውን ምልከታ ለአምባሳደሯ አብራርተዋል፡፡
በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ወ/ሮ ኢቶ ታካኮ ሀገራቸው ጃፓን ኢትዮጵያ ከድህነት ለመላቀቅ የምታደርገውን ጥረት ለማገዝ ለበርካታ አመታት ሰፊ የፋይናንስ እና የቴክኒክ ድጋፍ ስታደርግ መቆየቷን ገልጸው ይሄው ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡
ጃፓን በአፍሪካ ካሏት የዲፕሎማሲ ግንኙነት ለኢትዮጵያ ልዩ ትኩረት የምትሰጥ መሆኗን የገለጹት አምባሳደሯ በኢትዮጵያ ሰላም እና ኢኮኖሚያዊ እድገት እንዲረጋገጥ ሀገራቸው አቅም በፈቀደ ሁሉ ድጋፍ እንደምታደርግ ገልጸዋል፡፡
ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ
