ዜና ነ.እ.ፓ

አዳዲስ ዜናዎችን ይከታተሉ!አዳዲስ ዜናዎችን ይከታተሉ!

Submitted by contenteditor@… on Wed, 06/24/2020 - 16:09

የነጻነት እና እኩልነት ፓርቲ ሀረር ቅርንጫፍ ኮቪድ 19ን ለመከላከል በሀረር ከተማ የተቀናጀ የድጋፍ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡

በዛሬው እለት በተጀመረው የጸረ ኮሮና እንቅስቃሴ ስለ ቫይረሱ የግንዛቤ ማስጨበጫ መልዕክቶች፣ የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ማስክ፣ የንጽህና መጠበቂያ እቃዎች፣ እና ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው የህብረተሰብ አባላት የምግብ ቁሳቁሶች ድጋፍ ተደርጓል፡፡

ለፕሮግራሙ መሳካት ከፍተኛ ትብብር ላደረጉ የሀረሪ ክልል የመንግስት መስሪያ ቤቶች ነእፓ የላቀ ምስጋና ያቀርባል፡፡

ፓርቲው የኮቪድ 19 እንቅስቃሴውን በሌሎች ክልሎችም አጠናክሮ ይቀጥላል፡፡

ሰኔ 13፣ 2012

ነጻነት እና እኩልነት ፓርቲ ሀረር ቅርንጫፍ

ሀረር

news image
News Category