ዜና ነ.እ.ፓ

አዳዲስ ዜናዎችን ይከታተሉ!አዳዲስ ዜናዎችን ይከታተሉ!

Submitted bycontenteditor@… onThu, 12/17/2020 - 12:00

የኢሶዴፓ የድርጅት ጉዳይ እና የፓርቲው ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሉምባ ታደሰ ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ ዋና መስሪያ ቤትን የጎበኙ ሲሆን ከነእፓ ሊቀመንበር ከዶ/ር አብዱልቃድር አደም ጋር ሁለቱ ፓርቲዎች በትብብር መስራት በሚችሉብት እድሎች ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡

ዶ/ር አብዱልቃድር ሀገራችን ካሉባት ውስብስብ የፖለቲካ ችግሮች በአጭር ጊዜ ተላቃ ለማየት የፖለቲካ ፓርቲዎች ተቀራርበው መስራት እንዳለባቸው ነእፓ በጽኑ የሚያምን መሆኑን ገልጸው፣ ከኢሶዴፓ ጋር በጋራ ሀገራዊ አጀንዳዎች ዙሪያ በትብብር ለመስራት ፍላጎት እንዳለው ገልጸዋል፡፡

አቶ ሉምባ ታደሰ በበኩላቸው ፓርቲያቸው በፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል በቅንጅት መስራት ለኢትዮጰያ ሰላም እና አንድነት ከፍተኛ ፋይዳ አለው ብሎ እንደሚያምን ገልጸው፤ ለዚህም ከፓርቲያቸው (ኢሶዴፓ) ጋር ተቀራራቢ ፕሮግራም እና አስተሳሰብ ካላቸው፣ በህዝቦች መካከል አንድነት፣ ወንድማማችነት እና ሰላም እንዲሰፍን ከሚሰሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በትብብር ለመስራት ጥልቅ ፍላጎት ያለው መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ሁለቱ ኃላፊዎች በ2013 ይካሄዳል ተብሎ ከሚጠበቀው ጠቅላላ ምርጫ አንጻር ፓርቲዎቻቸው በጋራ መስራት በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ቀጣይ ምክክር ለማድረግ በመስማማት ውይይታቸውን አጠናቀዋል፡፡

ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ

አዲስ አበባ፡፡

news image
News Category