ዜና ነ.እ.ፓ

አዳዲስ ዜናዎችን ይከታተሉ!አዳዲስ ዜናዎችን ይከታተሉ!

Submitted bycontenteditor@… onWed, 12/23/2020 - 09:59

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የአዋጅ ቁጥር 1162/2011 እና በቦርዱ ፓርቲዎች ማሟላት ሚገባቸው ግዴታዎች በሚደነግገው መመሪያ መሰረት ውሳኔዎችን ሰጥቷል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በአዋጅ 1162/2011 እንዲሁም ፓርቲዎች ማሟላት የሚገባቸውን ግዴታዎች በሚደነግገው መመሪያ 03 መሰረት የተመዘገቡ እና በሂደት ላይ ያሉ ፓርቲዎች በአዲሱ አዋጅ ላይ የተቀመጡ መስፈርቶችን ማሟላታቸውን የማጣራት ስራ ሲያከናውን እንደነበር ይታወቃል፡፡ በዚህም ሂደት

1- ሁሉም ፓለቲካ ፓርቲዎች ማሟላት ያለባቸውን መስፈርቶች በጽሁፍ እንዲደርሳቸው እንዲሁም ማምጣት ያለባቸውን ተጨማሪ የመስራች ፊርማ ቁጥር በመጥቀስ እንዲያቀርቡ ተጠይቀዋል፡፡ በዚህም መሰረት ማሟላት ያለባቸውን ሰነዶች ያላቀረቡ 26 ፓርቲዎች ተሰርዘዋል፡፡

2- የመስራች አባላትን ያቀረቡ ፓርቲዎች መካከል ሳምፕል በመውሰድ በሁሉም ክልሎች እና ሁሉም ወረዳዎች የመስራች አባላትን ማጣራት ስራ አከናውኗል፡፡ ስራው የተከናወነው በቦርዱ የክልል ቅርጫፍ ጽህፈት ቤቶች አማካኝነት ሲሆን በዚህም መሰረት በሁሉም ወረዳ ላይ የቦርዱ ባለሞያዎች በግንባር በመገኘት የነዋሪነት ማረጋገጫ ለመስጠት ስልጣኑ ካላቸው የአስተዳደር አካላት ጋር በመተባበር መስራች አባላት እውነተኛነት እና መረጃዎችን ትክክለኛነት አረጋግጠዋል፡፡ በዚህ ሂደት ያጋጠሙ ችግሮች

• መረጃዎች በትክክል ተሞልተው አለምጣታቸው( የማይታወቅ ወረዳ፣ ትክክለኛ ያልሆነ የወረዳ የቀበሌ… ወዘተ ስም)

• የታችኛው እርከን አስተዳደር መረጃ አያያዝ ችግር የተነሳ ማጣራቱ ረጅም ጊዜ መውሰዱ (መታወቂያ ቁጥር፣ የቤት ቁጥር መረጃዎች አለመሟላት)

• በፓርቲዎች በኩል የተጓደሉ መረጃዎች ሲኖሩ በአጭር ጊዜ አሟልቶ ያለማቅረብ ችግሮች

• በኮቪድ 19 ወረርሽ የተነሳ የሰራተኞች እጥረት በቦርዱ በኩል በሚገባው ፍጥነት ማጠናቀቅ አለመቻል

በዚህም የተነሳ የማጣራት ሂደቱ ረጅም ጊዜ ከመውሰዱም በተጨማሪ በሂደቱ የተገኘው የማጣራት ውጤት ቦርዱ በፈለገው መንገድ ሊሆን አልቻልም፡፡ እንደአዲስ አበባ ባሉ የአስተዳደር አካላት የመስራች ፊርማን ለማጣራት ባልቻሉበት ሁኔታ ፓርቲዎች እንዳቀረቡት ትክክለኛ ፊርማ እንዲቆጥር ተደርጓል፡፡

ከዚህም በመነሳት 35 በመቶ በላይ መስራች ፊርማቸው ትክክል የሆኑ ፓርቲዎችን ምዝገባ ለማጽደቅ የወሰነ ሲሆን ከ35 በመቶ በታች የሆኑ ትክክለኛ ፊርማ ያመጡ እና የተለያዩ በቦርዱ የተጠየቁትን መስፈርት ያላሟሉ ፓርቲዎችን እንዲሰረዙ ወስኗል፡። በዚህም መሰረት

የመስራች ፊርማ ናሙና ማረጋገጫ ከ35 በመቶ በታች በመሆኑ የተሰረዙ ፓርቲዎች ዝርዝር የሚከተለው ነው

1. የአማራ ሕልውና ለኢትዮጵያ አንድነት - የመሥራች አባላት ናሙናን አስመልክቶ በተደረገው ማጣሪያ 24% ያገኘ

2. የኦሮሞ አንድነትና ዴሞክራሲ የፌዴራል የሠላም ለውጥ ፓርቲ - የመሥራች አባላት ናሙናን አስመልክቶ በተደረገው ማጣሪያ 25% ያገኘ

3. የኦሮሞ አቦ ነጻነት ግንባር - የመሥራች አባላት ናሙናን አስመልክቶ በተደረገው ማጣሪያ ከ10% ያገኘ

4. የኦሮሞ ነፃነት አንድነት ግንባር - የመሥራች አባላት ናሙናን አስመልክቶ በተደረገው ማጣሪያ ከ4% ያገኘ

5. የተባበሩት ኦሮሞ ነፃነት ግንባር - የመሥራች አባላት ናሙናን አስመልክቶ በተደረገው ማጣሪያ 33% ያገኘ

6. የኦሮሞ ነፃነት ዴሞክራሲያዊ ግንባር - የመሥራች አባላት ናሙናን አስመልክቶ በተደረገው ማጣሪያ 24% ያገኘ እና በቦርዱ በተሰጠው የጊዜ ገደብ መሠረት ጠቅላላ ጉባኤ ባለማካሄድ

7. የኦሮሚያ ነፃነት ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ - የመሥራች አባላት ናሙናን አስመልክቶ በተደረገው ማጣሪያ 14% ያገኘ እና በቦርዱ በተሰጠው የጊዜ ገደብ መሠረት ጠቅላላ ጉባኤ ባለማካሄድ

8. የኢትዮጵያዊያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ - የመሥራች አባላት ናሙናን አስመልክቶ በተደረገው ማጣሪያ 23% ያገኘ

9. ዱቤና ደገኒ ብሔረሰብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ - የመሥራች አባላት ናሙናን አስመልክቶ በተደረገው ማጣሪያ 5% ያገኘ

10. የአገው ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ- የመሥራች አባላት ናሙናን አስመልክቶ በተደረገው ማጣሪያ 19% ያገኘ

11. የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ሕብረት - የመሥራች አባላት ናሙናን አስመልክቶ በተደረገው ማጣሪያ 18% ያገኘ

12. የመላው ኢትዮጵያዊያን ብሔራዊ ንቅናቄ - የመሥራች አባላት ናሙናን አስመልክቶ በተደረገው ማጣሪያ 28% ያገኘ

13. የኦሮሞ ብሔራዊ ኮንግረስ - የመሥራች አባላት ናሙናን አስመልክቶ በተደረገው ማጣሪያ 18% ያገኘ

14. የኦሮሚያ ነፃነት ብሔራዊ ፓርቲ -የመሥራች አባላት ናሙናን አስመልክቶ በተደረገው ማጣሪያ 19% ያገኘ

15. ኅብረት ለዲሞክራሲና ለነፃነት - የመሥራች አባላት ናሙናን አስመልክቶ በተደረገው ማጣሪያ 17% ያገኘ

16. የሱማሌ አርበኞች ፓርቲ- የመሥራች አባላት ናሙናን አስመልክቶ በተደረገው ማጣሪያ 17% ያገኘ

17. የአፋር አብዮታዊ ፓርቲ- የመሥራች አባላት ናሙናን አስመልክቶ በተደረገው ማጣሪያ 9% ያገኘ

18. የሱማሌ ክልላዊ ዴሞክራሲያዊ ኅብረት- የመሥራች አባላት ናሙናን አስመልክቶ በተደረገው ማጣሪያ 3% ያገኘ

19. ምክክር ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፓርቲ- የመሥራች አባላት ናሙናን አስመልክቶ በተደረገው ማጣሪያ 32% ያገኘ

20. የወይኽምረ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ- የመሥራች አባላት ናሙናን አስመልክቶ በተደረገው ማጣሪያ 33% ያገኘ

ከመስራች አባላት ናሙና ትክክለኛነት ማጣራት ውጪ በሆነ መስፈርት የተሰረዙ

21. የኢትዮጵያ ሰላማዊ የዴሞክራሲያዊ ፓርቲ - የመስራች አባላት ብዛትና ስብጥር ባለማሟላት እና በቦርዱ በተሰጠው የጊዜ ገደብ መሠረት ጠቅላላ ጉባኤ ባለማካሄድ

22. አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ- የመሥራች አባላት ብዛትና ስብጥር ባለማሟላት እና በጠቅላላ ጉባኤ ምልአተ ጉባኤ ባለማሟላት

23. የኢትዮጵያ ኅብረ ሕዝብ ብሔራዊ ንቅናቄ - የመሥራች አባላት ብዛትና ስብጥር ባለማሟላት

24. ነፀብራቀ አማሐራ ድርጅት - በቅጹ ላይ በግልጽ ቢቀመጥም 2,691 የፓርቲውን መሥራች አባላት የአያት ስም አሟልቶ ባለማቅረብ

25. የፊንፊኔ ሕዝቦች አንድነት ለፍትህና ለዴሞክራሲ - የመሥራች አባላት ብዛት እና ከቦርዱ በተሰጠው አስተያየት መሠረት በሰነዶች ላይ ማስተካከያ ባለማድረግ

26. ሐረሪ ሪቫይቫል ንቅናቄ - በቦርዱ በተሰጠው የጊዜ ገደብ መሠረት ጠቅላላ ጉባኤ ባለማካሄድ

በተለያዩ ምክንያቶች ማብራሪያ እንዲሰጡ ወይም አሟልተው እንዲያቀርቡ የተወሰነ እና የማጣራት ሂደታቸው ያልተጠናቀቀ

1. ኅብር ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ

2. ሐረሪ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት

3. አፋር ነፃ አውጭ ግንባር ፓርቲ

4. የጉሙዝ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ

5. የአፋር ሕዝብ ፓርቲ

6. የኦሮሚያ ብሔራዊ ፓርቲ

7. የመላው ኢትዮጵያዊያን አንድነት ድርጅት ( መኢአድ)

8. ጋሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ

9. የወለኔ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ

10. መላው ኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ

11. የሲዳማ ብሔራዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ

12. የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር (ኦብነግ)

የማጣራት ሂደታቸው የተጠናቀቀ ፓርቲዎች ዝርዝር

1. የኦሮሞ ነፃነት ንቅናቄ - 51%

2. ቅማንት ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ - 57%

3. የሲዳማ አርነት ንቅናቄ -78%

4. የጌዲዮ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት- 93%

5. የጋምቤላ ህዝቦች ፍትህ ሰላምና ልማት ዴሞክራቲክ ንቅናቄ -91%

6. የኢትዮጵያ ዴሞክራቲክ ህብረት- 48%

7. የምእራብ ሶማሌ ዴሞክራቲክ ፓርቲ - 97%

8. የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ - 69%

9. የአገው ብሔራዊ ሸንጎ - 45%

10. ካፋ አረንጓዴ ፓርቲ - 61%

11. የጋምቤላ ህዝብ ነጻነት ንቅናቄ - 94%

12. የአፋር አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት ግንባር- 49%

13. የኢትዮጵያ ነጻነት ፓርቲ- 37%

14. የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲ - 48%

15. #ነጻነት_እና_እኩልነት_ፓርቲ-48%

16. ሞቻ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ -72%

17. የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ- 79%

18. የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ- 43%

19. የቤኒሻንጉል ህዝብ ነጻነት ንቅናቄ ለሰላምና ለዴሞክራሲ ድርጅት - 48%

20. የአፋር ህዝቦች ፍትሃዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ- 53%

21. አዲስ ትውልድ ፓርቲ - 64%

22. የኢትዮጵያ ብሔራዊ አንድነት ፓርቲ - 38%

23. የዎላይታ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ግንባር - 99%

24. የቁጫ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ - 100%

25. የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ- 38%

26. የዎላይታ ብሔራዊ ንቅናቄ - 96%

27. ብልጽግና ፓርቲ - 78%

28. የኢትዮጵያ ህዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ- 39 %

29. የኦሮሞ ነጻነት ግንባር - 47%

30. የሲዳማ ሃድቾ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት - 71%

31. የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ- 45%

32. የጋምቤላ ህዝብ ነጻነት ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ -93%

33. እናት ፓርቲ -47%

34. ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ- 64%

35. ቦሮ ዴሞክራቲክ ፓርቲ ( በአዲሱ አዋጅ ቀድሞ የተመዘገበ)

36. ዓረና ትግራይ ለዴሞክራሲ ሉአላዊነት (ከማጣራቱ ቀድመው የፊርማ መስፈርት ያጠናቀቁ)

37. የአርጎባ ብሔረሰብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ( አነስተኛ ቁጥር ያለው ብሔረሰብ ፓርቲ)

38. የአርጎባ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት ( አነስተኛ ቁጥር ያለው ብሔረሰብ ፓርቲ)

39. የዶንጋ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት ( አነስተኛ ቁጥር ያለው ብሔረሰብ ፓርቲ)

40. የፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ መድረክ ( ግንባር በመሆኑ ፊርማ ማቅረብ የማይገባው)

የማጣራት ሂደታቸው የተጠናቀቀ ነገር ግን የቴክኒክ መስፈርቶች የቀሯቸው ፓርቲዎች

1. ህዳሴ ፓርቲ

2. ሳልሳይ ወያነ ትግራይ

3. የካፋ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ህብረት

4. የራያ ራዩማ ዴሞክራሲዊ ፓርቲ

5. የሲዳማ አንድነት ፓርቲ

6. አሲምባ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ

7. ብሔራዊ ባይቶ ዓባይ ትግራይ

ቦርዱ የወሰነ መሆኑን ለዜጎች፣ ለሚዲያ ማህበረሰብ አባላት እና ለሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ያሳውቃል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

ታህሳስ 13 ቀን 2013 ዓ.ም

news image
News Category